የኢንስቲትዩቱ የአስተዳደር ዘርፍ የ9ወራት እቅድ አፈጻጸም ተገመገመ። ***********መጋቢት 30/2017******
የኢንስቲትዩቱ የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እና የቴክኖሎጂ ልማት ተልዕኮዎችን ለማሳካት ቁልፍ ሚና ያለው የአስተዳደር ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
የአስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አዋቶ በመድረኩ በተለይም የተስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት በቀሪ ወራት ውጤት ለማስመዝገብ ያለመ ውይይት ተካሂዷል ብለዋል።
ሁሉም ስራአስፈጻሚዎች ሪፖርታቸው አቅርበው መገምገሙን የገለጹት አቶ ኤልያስ ለማሳያነት የሚከተሉትን ጠቅሰዋል።
የተማሪዎች ምግብና መኝታ ቤት አገልግሎት ጥራት የማሻሻል ስራ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ሠልጣኞች የተቋሙን ደንብና ግዴታዎች እንዲያከብሩ ሊሰራ እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል
ከሠውሐብት ልማት አንጻር የሠራተኞችን መረጃ በሲስተም የማስገባት ስራ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የመመረተ ልማት ጥገና እና የአቅርቦት ጉዳይ ሌላው በትኩረት የተነሳ ሐሳብ ሲሆን ሁሉም የሥራ ክፍሎች በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸውና ተቋሙ ያቀዳቸው የልማት ስራዎችሊያሳኩ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ የሚያዘጋጃቸው አህጉር አቀፍ እና አገርአቀፍ ፕሮግራሞችን ለማሳካት፣ ለክህሎት ኢትዮጵያ የፈጠራ ፕሮግራም አስፈላጊ ግብአቶች የማማሟላት ስራ ተጠናክሮ እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።