ኢንስቲትዩቱ በሊፍት ገጠማ እና ጥገና መስክ የሠለጠነ የሰውሀይል ማፍራት የሚያስችል ስምምነት ከዳን ሊፍት ጋር ተፈራረመ። ********ሚያዚያ 2/2017*******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ከዳን ሊፍት ባለቤትና ስራአስኪያጅ ኢንጂነር ዳንኤል መብራህቱ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ዶ/ር ብሩክ በስምምነቱ ላይ እንደገለጹት በአገር ውስጥ የሊፍት ገጠማ እና ጥገና በአብዛኛው በልምድ በሚሰሩ ሙያተኞች እየተሰራ መሆኑን፣ በዚያም ላይ በቂ ሙያተኛ አለመኖሩን አንስተው የተቋማቱ ስምምነት ይህንን ይፈታል ብለዋል።
በሁለቱ ተቋማት ትብብር የሚሰለጥኑ ዜጎች ከአገር ውስጥ ገበያም ባሻገር በዘርፉ የሰለጠነ የሰውሀይል ለውጭ አገር ገበያ ለመላክ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በአገራችን በሊፍት ማምረትና ገጠማ ከ25 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ዳን ሊፍት ክህሎቱን ለብዙዎች ለማድረስ ፍላጎት እንዳለው ኢንጂነር ዳንኤል ገልጸው ኢንስቲትዩቱ ለዚህ አስቻይ ተቋም መሆኑን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል።





