ኢንስቲትዩቱ ለአገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የክህሎት ባንክ ገንብቶ አስመረቀ *******ሚያዚያ 1/2017***************
የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የገነባውን ለአገራችን የመጀመሪያ የሆነ እና የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን ከተጠቃሚው ጋር የሚያስተሳስር የክህሎት ባንክ መርቀው ከፍተዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪው ዙር የሰመርካምፕ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችም የመስሪያ ቦታ አስረክቧል፡፡
ክብርት ሚንስትር በምረቃ እና በመስሪያ ቦታ ርክክብ ሥነስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዲጂታል ደረጃ ተልሞት የነበር የክህሎት ባንክ ኢንስቲትዩቱ በተግባር ተርጉሞት አሳይቶናል ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የዘርፉን የለውጥ እሳቤ በተሳካ ሁኔታ እየፈጸም ያለ ተቋም መሆኑን የገለጹት ክብርት ሚንስትሯ የቴክኖሎጂ ባንክ በርካታ ትምህርት የተገኘበት እንደሆነ እና ይህ ባንክ ለአገራችን የፈጠራ ሥራን የሚያበረታታ ትልቅ አቅም የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በበኩላቸው ይህ የክህሎት ባንክ የወለውጥ እሳቤ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር ብሩክ አያይዘውም በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በተለይም በክህሎት ልማቱ ከተቀረጹ የለውጥ እሳቤዎችን ለማሳካት እየተጋ ያለ ኢንስቲትዩት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሰመርካምፕ ፕሮግራም የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ተመርተው ወደገበያው እንዲገቡ ከሚስፈልጋቸው መካከል የመስሪያ ቦታ አንዱ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ባለው አቅም ለተወሰኑ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ማዘጋጀቱን ጠቅሰው ድጋፉ ቀጣይነት እንዳለውም ቃል ገብተዋል፡፡