የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባቸው የልህቀት ማዕከላት አፈጻጸም የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እና ማኔጅመንት አባላት በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በምሥራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽንና ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት (EASTRIP) የሚገነቡ የልህቀት ማዕከላት ግንባታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በዚህም ግንባታዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ እየተሰራ ያለው ስራ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በቀጣይ ቀናት የግንባታ አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርታቸው ቀርቦ እንደሚገመገም ዶ/ር ብሩክ ገልጸዋል።





