Participants of Pan African Youth Leadership Conference visited the institute.
Participants of Pan African Youth Leadership Conference visited the institute.
*******መጋቢት 26/2017**********
The director of the institute Dr. Biruk Kedir welcomed the participants and made a statement about the institute and our country’s skill development.
“Skills are essential to make a prosperous Africa a reality” said the director general said the institute is striving to be a skill center not only for the citizens of our country but also for all Africans.
He stated that he is giving free training opportunities to South Sudan and Somaliland citizens among East African countries. He also noted that he is working in cooperation with other countries in the field of coaches development.
Dr. Biruk said that Ethiopia will work to unite our African brothers and sisters with Pan African spirit through technology innovation and skill development.
የፓን አፍሪካ የወጣቶች አመራር ጉባኤ ተሳታፊዎች ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ
*******መጋቢት 26/2017**********
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ተሳታፊዎች ተቀብለው ያስጎበኙ ሲሆን ስለኢንስቲትዩቱ እና ስለአገራችን የክህሎት ልማት ገለጻ አድርገዋል፡፡
‹‹የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ ክህሎት ወሳኝ ነው›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ለአገራችን ዜጎች ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪካዊያን የክህሎት ማዕከል ለመሆን እየተጋ ነው ብለዋል።
ከምሥራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ለደቡብ ሱዳንና ለሶማሌላንድ ዜጎች ነጻ የስልጠና እድል እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው ከሌሎች አገራት ጋርም በአሰልጣኞች ልማት መስክ በትብብር እየሰራ ይገኛል ብለዋ፡፡ እንደአገር በቴክኖሎጀ ፈጠራ መስክ ከተለያዩ አፍሪካዊ አገራት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
‹‹ክህሎት አስተሳሳሪ ነው›› ያሉት ዶ/ር ብሩክ፣ ኢትዮጵያ አፍሪካዊ እህት ወንድሞቻችንን በፓን አፍሪካን መንፈስ ዳግም በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በክህሎት ልማት ለማተሳሰር ትሰራለች ብለዋል፡፡