Shantex Garmite Manufacturing has graduated the trainees we trained in collaboration with the institute.

Shantex Garmite Manufacturing has graduated the trainees we trained in collaboration with the institute.
******** MARCH 23/2017*****
The director of FDRE Technical and Vocational Training Institute Dr. Biruk Kedir has attended the graduation of Shantex Garmite Manufacturing trainees, said that the institute is working to support the manufacturing industry of our country by producing skilled citizens.
The institute is working with Tianjin University of Technology and Education and various Chinese companies, in addition to vocational training, the institute has also said that it is working with the Tianjin Technology and Education University and various Chinese companies to improve their language skills.
It was announced at the inauguration that the institute’s confucius school and luban workshop gave training courses.
Chinese embassy representative, Tianjin university of education and technology, Luban workshop representatives were present at the inauguration. It is stated that capacity building trainings will continue.
Finally Shantex Garmite Manufacturing has visited Ethiopia.
ሻንቴክስ ጋርመይት ማኑፋክቸሪንግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመረቀ።
********መጋቢት 23/2017*****
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በሻንቴክስ ጋርመይት ማኑፋክቸሪንግ የሰልጣኞች ምረቃ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ኢንስቲትዩቱ በክህሎት የበቁ ዜጎችን በማፍራት የአገራችንን የማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ለመደገፍ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከቲያንጂን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና ከተለያዩ የቻይና ካምፓኒዎች ጋር በሚሰራው ስራ ዜጎች ከሙያ ስልጠናዎች በተጨማሪ የቋንቋ ችሎታቸውን እንዲያሳድጉ መሠራቱንም ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ የኮንፊሺየስ ት/ቤት እና የሉባን ወርክሾፕ ስልጠና ስልጠናዎችን መስጠታቸው በምረቃው ላይ ተገልጿል።
በምረቃው ላይ የቻይና ኤምባሲ ተወካይ፣ የቲያንጂን ትምህርትና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ የሉባን ወርክሾፕ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
በመጨረሻም ሻንቴክስ ጋርመይት ማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያ ጉብኝት አካሂደዋል።