ኢንስትዩቱን ከኢንደስትሪ ጋር በጥናትና ምርምር ስራዎች የማስተሳሰር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡ *********መጋቢት 17/2017 ዓ.ም***********

የኢንስቲትዩቱ 20ኛው ሳምንት የጥናትና ምርምር ሴሚናር በተግባር በተፈተሹ ሁለት የምርምር ስራዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሂዷል፡፡
ውይይቱን ያስጀመሩት የጥናትና ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) እንዳሉት በኢንስቲትዩቱ የሚሰሩ ጥናትና ምርምር ስራዎች ከኢንዱስትሪ ጋር የተሳሰሩ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
ይህም ‘’ቴክኒክና ሙያ ለኢንዱስትሪው፣ ኢንዱስትሪው ለቴክኒክና ሙያ’’ የሚለውን የትስስር መርህ ተግባራዊ ማድረግ ያስችላል ብለዋል።
ዶ/ር ሀብታሙ አያይዘውም በኢንስቲትዩቱ የሚለሙ ድረገጾች የዘርፉን አገልግሎትች የማዘመንን እሳቤ ተግባራዊ ለማድረግ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው የአገርበቀል ክህሎትችን መረጃ ለመሰነድ የተዘጋጀውን ድረገጽ በማሳያነት አንስተው ተናግረዋል።
በዕለቱ የመጀመሪው የምርምር ጽሑፍም ከዳሽን ቢራ ፋብሪካ በመጡ ባለሙያ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በቢራ ፋብሪዎች ውስጥ በምርት ሂደት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ዝገት በማስወገድ ጤናን፣ የአካባቢ ንጽህናን ማሻሻል በመቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተዘጋጀ የምርምር ስራ ነው።
አቅራቢው የቀድሞ የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኝ እና በአሁኑ ጊዜ በዳሸን ቢራ ፋብሪካ ሙያተኛ የሆኑት አቶ ገመቹ ደራራ ሲሆኑ Analysis of Corrosion Damage Phenomena in316L Stainless Steel Contacting with Beer በሚል ርዕስ አቅርበውታል።
ሌላኛው በዕለቱ ለውይይት የቀረበው የምርምር ጽሑፍ የአገር-በቀል ዕውቀቶችን ማከማቸት የሚያስችል የኦንላይን ሲስተምን የተመለከተ ሲሆን Developing an Online TVET-Related IKS Repository System በሚል ርዕስ ለውይይት ቀርቧል፡፡
በአሰልጣኝ መሳይ ዳንኤል እና ሰይድ መሃመድ የበለጸገው ሲስተሙ፤ ሰዎች ባሉበት ሆነው አገር በቀል ዕውቀቶችን እንዲያከማቹ የሚያስችል ሲሆን ለስልጠና ተቋማት ትልቅ መረጃ ሰጪ እንደሚሆንም አልሚዎቹ አብራርተዋል፡፡