ኢንስቲትዩቱ በዓመቱ የያዛቸው እቅዶች እንዲሳኩ የሪፎርም ቡድኖች ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለጸ። ***********መጋቢት 11/2017*******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በኢንስቲትዩቱ ሥራ ላይ ያሉ የሪፎርም ቡድኖችን የቀጣይ ወራት የተግባር መመሪያ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ብሩክ በኦረንቴሽን ላይ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በሪፎርም እሳቤ አቅዶ በመተግበር አመርቂ ውጤት ሲያስመዘግብ መቆየቱን ገልጸዋል።
ባለፉት 9 ወራት ብቻ እንኳን በርካታ ውጤቶችን መመዝገባቸውን ገልጸው በቀጣይ ወራት በላቀ አፈጻጸም በመፈጸም የተያዙትን የዓመተ ልህቀት 2 ግቦች ማሳካት ይገባል ብለዋል።
ለ 9 የሪፎርም ቡድኖች ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ እንደመሪ ተቋም ለአገራችን የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሞዴል ለመሆን መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።