አስራዘጠነኛው ሳምንት የጥናትና ምርምር ጉባኤ በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።
አስራዘጠነኛው ሳምንት የጥናትና ምርምር ጉባኤ በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።
***መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ********
በኢንስቲትዩቱ በየሳምንቱ እየተካሄደ ያለው መደበኛው የጥናትና ምርምር ጉባዔ በ19ኛ ሳምንት ሴሚናር ሁለት አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።
ውይይቶቹ የአሰልጣኞች የምርምር የፈጠራ ችሎታ ይበልጥ እያጎለበቱ እንደሆነም ገልጸዋል።
የደረጃ 7 ሰልጣኞች በሳምንታዊ ሴሚናሮች ላይ ሳያቆራርጡ መሳተፋቸውም በቀጣይ ዘርፉን የሚለውጡ የምርምር ውጤቶች በስፋት እንዲገኙ ምቹ ሁኔታ ያመቻቻል ብለዋል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በኢንስቲትዩቱ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች የዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የሥልጠናን ጥራትና አግባብነት ለማሳካት የሚያግዙ ቁልፍ ተግባራት ናቸው ብለዋል።
በዕለቱ ሁለት ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው ‘’ Exploring Bamboo as a Sustainable Construction Material for Affordable Housing in Ethiopia: Challenges and Opportunities ’’ በሚል ርዕስ በአሰልጣኝ ቻላቸው ቦጋለ ቀርቧል።
ሌላኛው የጥናትና ምርምር ስራ በኢንስቲትዩቱ የድህረ-ምረቃ ሰልጣኝ ወንድማገኝ ታምሩ የቀረበ Effects of Feed Moisture, Barrel Temp. ,and Blending Ratio on the Physiochemical Properties, Functional Properties, and Sensory Quality of Corn, Pea, and Carrot Extradite የሚል ሲሆን አልሚ የሆነ ስናክ ከበቆሎ፣ አቴርና ካሮት በመስራት የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።










