ኢንስቲትዩቱ ለጋምቤላ ክልል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ኢንስቲትዩቱ ለጋምቤላ ክልል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
**********የካቲት 18/2017*******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የጋምቤላ ክልል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚያስችል የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ለአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡቶንግ ኡጁሉ አስረክበዋል።
የኢንስቲትዩቱ ሀላፊዎች በጋምቤላ ክልል በነበራቸው የስራ ጉብኝት ወቅት ማዕከሉን ለማጠናከር ድጋፍ እንዲያደርጉ ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን የዚያ አካል እንደሆነ ዶ/ር ብሩክ ገልጸዋል።
ዶ/ር ብሩክ አያይዘውም ኢንስቲትዩቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።