በዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ኢንስቲትዩቱን ጉበኙ፡፡ **** የካቲት 11/2017 ዓ.ም*****
በዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና የሰው ሀብት ልማት፣ ጤና፣ ትምህርት እና የማህበራዊ ደህንነት ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ሚስተር ዳንኤል ደሊስኪ ኢንስቲትዩቱን ጎብኝተዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም በጥናትና ምርምር ተልዕኮዎችን እየተመጣ እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው ለተልዕኮው ስኬት ዓለም ባንክ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ያስተናገዱ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ እየሰራቸው ያላቸውን ስራዎች ገልጸው የዓለም ባንክ በተለያዩ ፕሮጀክቶች በኩል እያደረገ ያለው ድጋፍ ብዙ ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል፡፡
የባንኩ ድጋፍ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ እያገዘ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ከዚህም ባሻገር ዲጂታይዘሽንን ለማረጋገጥ፣ ቀጠናዊ ትስስር እንዲጠናከር በማድረግ እና የስራ እድል ፈጠራ ላይ አበረታች ስራ መሰራቱን አንስተዋል፡፡
በባንኩ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬከተሩ ሚስተር ዳንኤል በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ለጎረቤት አገራት ዜጎች የስልጠና ዕድል በመፍጠር እየሰለጠነ መሆኑን አድንቀው የኢንስቲትዩቱና የግሉ ዘርፍ ትብብር እና በስልጠና ፕሮግራሞች ጥራት መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ የወጣቶች አህጉር መሆኗም ያስታወሱት ዳይሬክተሩ በሥልጠና ተቋማት ዲጂታል ክህሎት እንዲስፋፋ ባንኩ ሚናውን እንደሚወጣም ገልጸዋል፡፡
የባንኩ ድጋፍ በአጠቃላይ ወጣቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሴቶችን በመደገፍ የስልጠና ጥራትና ተደራሽነት እንዲሰፋ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
በሥነስርዓቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተሮች፣ የዓለምባንክ ሙያተኞች፣ የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል።