በዓለምአቀፍ ብየዳ ስልጠና ከዚህ ቀደም በቂ እድል ያላገኙትን ክልሎች ማዕከል ያደረገ ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡ *****************ጥር 20/2017********

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ማምረት እና የብየዳ ልህቀት ማዕከል በሦስተኛ ዙር ዓለምአቀፍ ብየዳ ከስድስት ክልሎች የተውጣጡ ሙያተኞችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባሳለፍነው ወር በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በነበራቸው የስራ ጉብኘት ወቅት ከለዩዋቸው የስልጠና ፍላጎቶች መካከል የብየዳ ስልጠና አንዱ ሲሆን ይህንንም ታሳቢ ያደረገ ዓለምአቀፍ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
በብየዳ ስልጠና ከዚህ ቀደም በቂ እድል ያልተሰጣቸውን አፋር፣ ሶማሌ፣ ሀረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልሎች የኮሌጅ አሰልጣኞች እና የኢንዱስትሪ ቴክኒሺኖች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡
በስልጠናው እየተሳተፉ ያሉ ሙያተኞች ስልጠናው ምርታማ እንደሚያደርጋቸው፣ ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጠርላቸው እንዲሁም ቴክኖሎጂ ፈጠራቸውን ጥራት እንደሚጨምርላቸው ተናግረዋል፡፡
ሚስባህ ሙሃመድ በአፋር ክልል የአፍሪካ እንጨት ውጤቶች ድርጅት ቴክኒሺያን ነው፡፡ ወጣቱ እንደሚለው ይህንን ስልጠና ማግኘቱ የተጨማሪ ክህሎት ባለቤት በመሆን በሙያው ተፈላጊ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡
በእንጨት ውጤቶች ስራ ውስጥ የብረት ስራዎች በሚያስፈልጉ ጊዜ ለሌላ ድርጅት ሰጥቶ ያሰራ የነበረው ድርጅቱ በአንድ ቦታ ስራውን አጠናቅቆ እንዲያቀርብ ያስችለዋልና ይህ ስልጠና ከግለሰቡ አልፎ ድርጅቱን እንደሚጠቅመው ይናገራል፡፡
በጋምቤላ ክልል ኦፔኖ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ ፍሰሃ ተስፋዬ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሐደሮ ቱንቶ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ አሰልጣኝ ምስጋና አበበ በበኩላቸው በተቋሞቻቸው የብየዳ ሙያ ማሰልጠኛ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን ቢኖሩም አሰልጣኞች ክህሎት ባለመጨበጣቸው ስልጠና ለመስጠት ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰው ይህን ስልጠና ማግኘታቸው ሁሉንም ማሽኖች ወደስራ ለማስገባት እና ጥራት ያለው ስልጠና ለመስጠት እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
የብየዳ ሙያ በየትኛውም ሙያ ላይ ላለ አሰልጣኝ እንደ አይሲቲ እውቀት ሁሉ መሰረታዊ እውቀት ነው የሚለው በሉሲ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ ከፈለኝ ገሰሰ ሲሆን የፈጠራ ሀሳቡን ወደ ተጨባጭ ምርት ለመቀየር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት ተናግሯል፡፡
የዓለምአቀፍ ብየዳ መሪ ስራአስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ዓለሙ ስልጠናው በሦስት የብየዳ መስኮች ማለትም በአርክ፣ በማግ እና በቲግ ዌልዲንግ እንደሚሰጥ ገልጸው ይህ ስልጠና ተቋማት ማሽኖቻቸውን ወደስራ ለማስገባት፣ አሰልጣኞች ጥራት ያለው ስልጠና እንዲሰጡ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡
ኢንደስትሪ ቴክኒሺኖች በብዛት በልምድ የሚሰሩበትን ሁኔታ በመቅረፍ ዘመኑ የደረሰበትን ክህሎት በማስጨበጥ ውጤታማ ስራ እንዲሠሩ ያስችላልም ብለዋል፡፡
ቲክቶክ @fdretvtistitute
+8
All reactions:

79