በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢንስቲትዩታችን የስፖርት ልዑካን ቡድን በተሳተፈባቸው ሁለት ውድድሮች ድል አስመዝግቧል።
በአሰልጣኝ ሰሎሞን ቱፋ የሚመራው የኢንስቲትዩታችን የእግር ኳስ ቡድን ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተፋልሞ 3ለ1 በሆነ ውጤት በመርታት ውድድሩን በድል ጀምሯል።
ከዚህም በተጨማሪ ሰልጣኛችን እየሩሳሌም ተሾመ ከ46ኪ/ግራም በታች የቴክዋንዶ ውድድር ተፋልማ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።