የኢንስቲትዩቱ 14ኛ ሳምንት የጥናትና ምርምር ሴሚናር በሁለት የጥናት ስራዎች ላይ ተመስርቶ ተካሄደ፡፡ ************ጥር 14/2017*******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት 14ኛ ሳምንት የጥናትና ምርምር ሴሚናር በኤሌክትሪክ መኪና ቴክኖሎጂ እና በመጪው ዘመን የሰለጠነ የሰው ሀይል የገበያ ፍላጎት ላይ ትኩረታቸውን ባደረጉ ሁለት ጥናቶች ላይ ተመስርቶ ተካሂዷል፡፡
ጥናቶቹም በዶ/ር ኢንጂነር ዮሴፍ ገሰሰ ‹‹Skills Demands in Electric Vehicles: International Perspectives በሚል ርዕስ የቀረበው እንዱ ሲሆን ሌላው ‹‹ Lessons Learned from Literature on Labor Demand Forecasting በሚል ርዕስ በዶ/ር ባንቻየሁ ግርማ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ሴሚናሩን በቪዲዮ መልዕክት የከፈቱት የጥናትና ምርምር እና ማህረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ኢንስቲትዩቱ ጥናትና ምርምሮችን ከኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች በተጨማሪ በተለያየ መስክ ዕውቀቱ ካላቸው ሌሎች ተመራማሪዎች ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ዕለት ከጀርመን ሀገር ጥናታቸውን ላቀረቡት ዶ/ር ኢንጂነር ዮሴፍ ገሰሰ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የኤሌክትሪክ መኪና ቴክኖሎጂ አገራችንን ጨምሮ በዓለምአቀፍ ደረጃ እየተስፋፋ የመጣ ዘርፍ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ሀብታሙ አዲስ እሳቤ በመሆኑ ተከታታይ ጥናቶችን በማጥናት የሚነሱ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ሀሳቦች መቅረፍ፣ ቴክኖሎጂዎችን ለመስራት መጣር ይገባል ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩታችንም ከዚህ አኳያ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ነው ብለዋል፡፡
ሌላው በዕለቱ የቀረበውን የመጪው ዘመን የሰለጠነ የሰው ሀይል የገበያ ፍላጎት ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ጥናት በመተመለከተ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው በመሆኑ ኢንስቲትዩታችን በትኩረት እየሰራ ነው እንዳለ ገልጸዋል።
ጥናቱ ስልጠና እና አቅም ግንባታ የሚኖረው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን አንስተው፤ በቀጣይም መሰል ጥናትና ምርምር ስራዎች እንደሚሰሩ አስገንዝበዋል፡፡
በጀርመን አገር በኤሌከትሪክ መኪና ቴክኖሎጂ ላይ እየሰሩ ያሉት እና በዘርፉ ዕውቀት እና ልምድ ያላቸው የሆኑት ኢንጂነር ዮሴፍ ገሰሰ (ዶ/ር) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቴክኖሎጂ የሚሻቸውን ክህሎቶች ከዓለምአቀፍ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ የዳሰሱበትን ጥናት Skill Demands in Electric Vehicles: International Perspectives በሚር ርዕስ አቅርበዋል።
በጥናታቸውም ዓለም ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ቴክኖሎጂ እየተሸጋገረ የሚገኝባቸውን ምክንያቶች፤ ይበልጥ ሊሰራባቸው ይገባል ያሏቸውን በዘርፉ ያሉ ችግሮችንም አንስተዋል።
በተለያዩ አገራት በአጫጭር እና በረጅም ጊዜ ስልጠናዎች እየተሰጡ ቢሆንም ዘርፉ አዲሰ እንደመሆኑ ገና ብዙ ሊሰራ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በፈጠረው ትስስር በጀርመን አገር ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት ለኢንስቲትዩቱ ሙያተኞች ስልጠና ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በመቀጠልም የኢንስቲትዩታችን ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ባንቻየሁ ጥናታቸውን አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡