የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች የኢንስቲትዩቱን አዳዲስ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ጎበኙ። ******ጥር 09/017ዓ.ም****
የኢንስቲዩቱ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ዛሬ የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም ከገመገሙ በኋላ በተቋሙ የውስጥ አቅም እየተከናወኑ ያሉ ልማታዊ ፕሮጀክቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በውስጥ አቅም ተሰርተዉ እየተጠናቀቁ የሚገኙ በግብርናው መስክ የተሰሩ ፕሮጀክቶች የታዩ ሲሆን እነዚህ ፕሮጀክቶች ለሰልጣኞች የተግባር ስልጠና ማዕከል ሆነው እንደሚያገለግሉ የሚያመርቷቸው ምርቶችም ለሠራተኛው በቅናሽ ዋጋ የምሸምትበት እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።
በተያያዘም ምቹ የስራ ከባቢን ለመፍጠር እየተሰሩካሉ መካከል ሰራተኞች ካፍቴሪያ እድሳት እና ዘመናዊ ወንበርና ጠረጴዛ ለመሟላት በእንጨት ስራ ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል አሠልጣኞች እየተመረቱ ያሉ ምርቶችን ተጎብኝተዋል። በውስጥ አቅም እነዚህን ምርቶች መስራት ትልቅ አቅም እየገነባን እንደሆነ ማሳያዎች እንደሆኑ ተገልጿል።
በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እየተገነቡ ያሉ የልህቀት ማዕከላት ሕንጻዎች ግንባታ በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እየተከናወኑ እንደሆነበጉብኝቱ መመልከት ተችሏል።
በኢንቲትዩቱ የተግባር ስልጠና እየሰጠ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምርቶችን የማማረት ተልዕኮ ተሰጥቶት የተመሠረተው ‘ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ልማት እንተርፕራይዝ’ እየተሰሰሩ ያሉ ተግባራትም ተብራርተዋል።
በኢንተርፕራይዙ ውስጥ ያለው አሮጌ ጎማዎችን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውለው እና 13 ማሽኖችን በተቋሙ ሙሉበሙሉ ተመርቶ የተተከለው ፋብሪካ ከሰራተኞች ብዙ አድናቆት ተችሮታል።
የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ባንክ መገንባት መቻሉ የተመሠገነ ሲሆን አፈጻጸሙም ወደመጨረሻ ምዕራፍ እንደደረሰ ታይቷል።
ከጉብኝቱ በኋላም ሀሳባቸውን ያጋሩ ጎብኚዎች በተመለከቱት ነገር መደነቃቸውንና ይህን የመሰለ ተግባራዊ ለውጥ የሚመሩ አመራሮችን አመስግነዋል። የበለጠ ውጤት ለማምጣትም ካለፈው ይልቅ በትጋት እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።