የኢንስቲትዩቱ ሐዋሳ ካምፓስ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻም ምገማ መድረክ አካሄደ። **ጥር 9/2017 ዓ.ም**
በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሀዋሳ ካምፓስ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሂዷል።
ባሳለፍነው የግማሽ ዓመቱ የመደበኛ እና የሪፎርም ተግባራት አፈፃፀም በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ተገኝ መሀደም የቀረበ ሲሆን የISO 9001:2015 የጥራት ስራ አመራር ትግበራ ሂደት አፈፃፀም በትግበራ ግብረ-ሃይሉ አስተባባሪአቶ ሙሉጌታ ጎንፋ ቀርቧል።
ተሳታፊዎችም የተገኙ ውጤቶች ላይ በቡድን ውይይቶች ጭምር ሰፊ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን የካምፓሱ ኃላፊ አቶ ፍፁም ግርማ ከተነሱ ጉዳዮች መነሻ የስራ አቅጣጫ ሰጥተው የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።