ኢንስቲትዩቱ ሠርቶ ያጠናቀቃቸውን የአቅመደካሞች ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረከበ። ********ታህሳስ 28/2017******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በየካ ክፍለከተማ ወረዳ 09 የሚገኙ የአቅመደካማ ቤቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ለተጠቃሚዎች አስረክቧል። ለበአል መዋያ ስጦታም አበርክቷል።
በርክክቡ ላይ የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐብታሙ ሙሉጌታ፣ የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሐኑ ረታ፣ የክፍለከተማው የወረዳ 09 ዋና ስራአስፈጻሚ አቶ ተድላ ታምራት እና በየደረጃው ያሉ ስራ ሀላፊዎችና ሙያተኞች ተገኝተው ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ሐብታሙ ሙሉጌታ የኢንስቲትዩቱ አንዱ ተልዕኮ የማህበረሰብ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ተልዕኮውን ለበርካታ ዓመታት አጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች በሚወስዱት ስልጠና በተግባር ውጤታማ መሆናቸውን ያሳዩበት ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸው በዚህ ፕሮጀክትም በግንባታ፣ በኤሌክትሪክ፤ በብየዳ እና በሌሎችም መስኮች ተሳትፈው ለውጤት አብቅተውታል ብለዋል።
የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሐኑ ረታ ኢንስቲትዩቱ ማህበራዊ ሐላፊነቱን እየተወጣ ያለ ተቋም በመሆኑ ሊመሠገን ይገባዋል ብለዋል። ላለፉት ዓመታት ከክፍለከተማው ጋር በቅርበት እየተባበረ መሆኑን በመግለጽ ስንተባበር የማንሻገረው ነገር የለም ብለዋል።