የኢንስቲትዩቱ ዓመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ። ********ታህሳስ29/2017********

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።
የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙልጌታን ጨምሮ አሠልጣኞችና ሠልጣኞች በተገኙበት በተጀመረው ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት ኢንስቲትዩቱ በክህሎቱ እና በአካላዊና ብቃቱ የጎለበተ ማህበረሰብ እንዲኖር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱን የሚመጥን ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት ማዘውተሪያ እንዲኖር እንሰራለን በማለት ዶ/ር ብሩክ ቃል ገብተዋል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ በኢንስቲትዩቱ የሚገኙ የቴክዋንዶ ሰልጣኞች ትርኢት ያሳዩ ሲሆን ኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ ፋካሊቲ ከሲቪል ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ጋር የእግር ካስ ውድድር አካሂደዋል። በዚህም ሲቪል ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ 1ለ0 አሸንፏል።