የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ልማት ተልዕኮ ከተቋም አልፎ ለአገር ምሳሌ እና ሞዴል የመሆን ተልዕኮ ነው፡፡ (ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ – ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር) *************ታህሳስ 16/2017***************
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ የኢንስቲትዩቱን የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግመዋል፡፡
በዘርፉ የተሰሩ የቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ስራዎች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከተገኙ ውጤቶች መካከልም በአገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆኑ የቴክሎጂ ልማት ፍኖተ-ካርታ የብዝሀ ምርት ፍኖተ-ካርታ የተዘጋጀ ሲሆን ሰነዶቹን የማጸደቅ ስራ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
ሪፖርቱ አያይይዞም ኢንስቲትዩቱ ከኢንደስትሪዎች ጋር በሰራው ትስስር የመደበኛ ስልጠና ፕሮግራም እና የክህሎት ኢትዮጵያ ሰልጣኞች የተግባር ስልጠና እና የኢንዱስትሪ ጉብኝት ማካሄድ ችለዋል፡፡ አሰልጣኞችም እነዲሁ የተግባር ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል፡፡
በኢንተርፕራይዝ ምስረታ ሂደትም ቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ኢንተርፕራይዝን እና በማጠናር ‹‹እያሰለጠነ ለማምረት›› ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገልጻል፡፡ ከዚህም በላይ ለማስፋፋት የተለያዩ ውጤታማ ልምዶች መቀመራቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ጸዳለ ያለፉት ስድስት ወራት በዘርፉ በርካታ ውጤታማ ተግባራት እንደተሰሩ ገልጸው በተለይም ቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ ኢንስቲትዩቱ በሰራው ስራ እንደ አገር ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን የመተካት፣ የአገር ምርት የመጠቀም ፍላጎትን የማሳደግ ትልቅ ለውጥ ታይቷል ብለዋል፡፡
ይሁንና የዘርፉ ተልዕኮ ከተቋም አልፎ አገር የመቀየር ሀሳብ ያለው በመሆኑ ከዚህ በላይ ሊሰራበት ይገባል ያሉ ሲሆን ስራዎችን ከተለመደ መንገድ ወጥቶ አዳዲስ እና ለውጥ የሚያመጡ አሰራሮችን መንደፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተቋም ውስጥ እና ከተቋም ውጪ የተጀማመሩ ለውጥ የሚያመጡ የቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ስራዎች ተጠናክረው ሊሰሩ እንደሚገቡ አሳስበዋል፡፡ ከዚህም መካከል ከተለያዩ ተቋማት የተሰጡ የቴክኖሎጂ ምርት ጥያቄዎችን በፍጥነት እያመረቱ ማቅረብ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩ እና አዳዲስ የሆኑ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በማዕድን ልማት፣ በኮንስትራክሽንና በሌሎችም መስኮች ያሉ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ሰርቶ ማጠናቀቅ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በMass Production ደረጃ ማፈጠን፣ የሰልጠኞች የስራ ፈጠራ ባህል ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ወ/ሮ ጸዳለ አያይዘውም በቀጣይ የቴክኖሎጂ ልማትን ከጥናትና ምርምር ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር የእሴት ሰንሰለት ትንተናዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ቲክቶክ @fdretvtistitute