ኢንስቲትዩቱ በውስጥ አቅም በሠራው ሥራ ከአገልግሎት ውጪ የነበሩ በርካታ ቁሳቁሶችን አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻሉ ተገለጸ። *****ታህሳስ 09/2017 ዓ.ም*******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በቢሮዎች፣ በስልጠና ክፍሎች፣ በተማሪዎች መመገቢያ ውስጥ በተለያየ ምክንያት ብልሽት ገጥሟቸው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ወንበሮችን በመጠገን ጥቅም ላይ የማዋል ስራ ማከናወኑ እና በዚህም ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።
የኢንስቲትዩቱ መሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ያስተባበረው ይህ ተግባር ከአገልግሎት ውጭ ያሉ 5 መቶ የሚደርሱ ወንበሮችን ወደስራ ለመመለስ የታለመ ነው ተብሏል።
እነዚህ ወንበሮችን ለመግዛት ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ያላነሰ ብር ያስወጣ እንደነበር የመሰረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጅማ ገልጸው ይህንን ወጪ ለመቆጠብ ብሎን ብቻ በመግዛት በስራ ክፍሉ ያሉ ሰዎች በሙያቸው ጥገና እያደረጉ ሲሆን ይህም 1 ሚሊዮን 170 ሺህ ብር ማትረፍ እንደሚያስችል ተናግረዋል።