ለኢንስቲትዩቱ አዲስ ሰልጣኞች የ5ሚሊየን ኮደርስ ኢንሼቲቭ ላይ መሠልጠን እንዲችሉ ገለጻ ተደረገ። *************ታህሳስ 12/2017********
የኢንስቲትዩቱ አዳዲስ ሰልጣኞች “ትውልድ ይማር፣ ትውልድ ይሰልጥን፣ ከዓለም ጋር ይፎካከር” በሚል እሳቤ ወጣቶች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን በማዳበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ለማድረግ እየተተገበረ በሚገኘው የ5ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ገለጻ ተካሂዷል።
ለዚህ ስልጠና በነፃ https://ethiocoders.et/ ድህረ ገፅ በመመዝገብ ስልጠናውን ኦንላይን መሰልጠን እንደሚችሉ ተገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በሦስት ዓመታት 5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስና በሠውሰራሽ አስተውሎት መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ ለማስቻል የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል።