ጥምር የስልጠና ስልትን በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ውስጥ ባህል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ። ***********ታህሳስ 3/2017***********
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጥምር የስልጠና ስልትን (Blended Training) በስፋት ለመተግበር የአሰልጣኞች ስልጠና የወሰዱ አሰልጣኞችን ተግባር ተኮር የሆነ የማንቂያ ስልጠና ሰጥቷል።
ጥምር የስልጠና ስልት ዘመኑ የሚጠይቀው አንዱ ስልት መሆኑን ያስገነዘቡት ዋና ዳይሬክተሩ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ውስጥ በውጤታማነት ለመፈጸም በዚህ ስልጠና እየተሳተፉ ያሉ እና በቀጣይም በተዋረድ ስልጠናውን የሚያገኙ አሰልጣኞች ትልቅ ሚና እንዲወጡ ከአደራ ጋር አሳስበዋል።
ኢንስቲትዩቱ የጥምር ስልጠና ለመስጠት ሰልጣኞችን አሳታፊ የሆኑ ኮርሶች በአሰልጣኞች ተዘጋጅተው በE-learning management system ይጫናሉ ያሉት ደግሞ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ናኦል አንበሴ ናቸው። ይህ ስልጠናም ጅምሩን ለማስፋት እና አሰልጣኞችን ለማነቃቃት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።
ስልጠናውን በኢንስቲትዩቱ በአካል እና በሳተላይት ተቋማት በቪዲዮ አማራጭ ተከታትለውታል።