ትብብር ለላቀ የቴክኒክና ሙያ ስኬት በቻይና የተለያየ ተቋማት ጋር በተደረገ ጉብኝት 4 ዋና ዋና ውጤቶች መመዝገባቸውን የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ገልፀዋል።

የሄናን ግዛት ላይ በተካሄደው Chinese+ Vocational Skills Conference ላይ በተመረጡ የሙያ መስኮች ላይ ከሄናን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በተለያዩ ሙያዎች ስልጠና ለማጠናከር ስምምነት መደረጉ የመጀመሪያው ውጤት ሲሆን
የሲቹዋን የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ጋር በተደረገ ስምምነት በታዳሽ ሀይል ( New Energy Technology) በተለይም በኤሌክትሪክ መኪኖች ጥገናና አጠቃቀም፣ ብየዳና ማኒፋክቸሪንግ ላይ ሙያተኞች ለማሰልጠንና የአሰልጣኝ- ሰልጣኝ ልውውጥ ለማድረግ ስምምነት መደረጉ ሌላው የጉብኝቱ ትሩፋት መሆኑን አንስተዋል።
ዶ/ር ብሩክ አያይዘውም ከኒያንጂንግ የሙያ ትምህርትና ኢንዱስትሪ ዩንቨርስቲ ጋር በተደረገ ውይይት በታዳሽ ሀይል ዘርፍ ስልጠና ለማጠናከርና ከ ቢዋይዲ BYD የመኪና አምራች ጋር ዩኒቨርስቲው እየተከተለ ያለው የተግባር ስልጠና እንደልምድ በመውሰድ በሀገራችን የኤሌክትሪክ መኪኖች የስልጠና ወርክሾፕ በማቋቋም ዙሪያ ልምድ ለመቅሰም ያለመ ስምምነት ተደርጓል ብለዋል።
ሌላው አራተኛው የትብብሩ ውጤት ከኒሳን የመኪና ፋብሪካና በጥምረት ከሚሰራው ሲቹዋን ኮሌጅ ጋር በመሆን በአውቶሞቲቭ ዘርፍ የጥምር ዲግሪ መርሀ ግብር ለተቋማችን ሰልጣኞች በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ስምምነቶች ተደርጓል።
በጉብኝቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድርና የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክተር ሀፍቶም ገ/እግዚአብሄር ተገኝተዋል።