መሠረቱን ጣሊያን ያደረገው ዩኒቨርሳል አርትና ዲዛይን ኢንስቲትዩት ሥራ ሀላፊዎች በኢንስቲትዩታችን ጉብኝት አደረጉ። ******ህዳር 13/2017****

መሠረቱን ጣሊያ አድርጎ በሲኒማ፣ በፋሽንና ዲዛይን ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራው ዩኒቨርሳል አርትና ዲዛይን ኢንስቲትዩት (Universal Art and Disign Institute) ኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን የፋሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና ለመደገፍ አብሮ መስራት ፍላጎት እንዳለው የኢንስቲትዩቱ ፕሬዚደንት ሂቸል ሌተሪ ገልጸዋል።
የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐብታሙ ሙሉጌታ በአቶ ሂቸል ሌተሪ የተመራ የሀላፊዎች ቡድንን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ውይይታቸውም ኢንስቲትዩቱ የጀመራቸውንና ለመጀመር ያቀዳቸውን የስልጠና መስኮች ለማጠናከር በጋራ መስራት በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ያተኮረ ነው። የአሰለሰጣኞችና ሠልጣኞች አቅም ግንባታ እና በዘርፉ ዘመኑ የደረሰባቸው ቴክኖሎጂዎች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ተገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በኢንስቲትዩቱ የአፓረል ፋሽን ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ጉብኝት አድርገው በሰልጣኞችና ሰልጣኞች በተሰሩ ፋሽን ምርቶች መደነቃቸውን ገልጸዋል።