የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ በ2017 ለኢንስቲትዩቱ ልህቀት ቁልፍ ሚና እንደሚወጣ የስልጠናና አቅም ግንባታ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሄር (ረ/ፕሮፌሰር) ገለጹ። ************ጥቅምት 25/2017************

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስልጠናና አቅም ግንባታ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሄር (ረ/ፕሮፌሰር) የዘርፉን የ2017 የስልጠናና አቅም ግንባታ ዕቅድ ተናባቢነቱ ላይ ግምገማ አካሂደዋል።
አካዳሚክ ዳይሬክተሮች፣ ፋካሊቲ ዲኖች፣ ትምህርት ክፍል ሀላፊዎች በገኙበት የተካሄደው ይህ ውይይት ተቋማዊ ልህቀትን ለማስመዝገብ የሚያስችል ዕቅድ ይዞ ለመቀጠል ያስችላል ብለዋል።
ይህንን የጋራ ውይይት ማካሄድ የዘርፉ ዕቅድ ከሌሎች ዘርፎች እቅድ ጋር ተመጋጋቢ እንዲሆን እንዲሁም እስከ ትምህርት ክፍል ድረስ ተናባቢ የሆነ ዕቅድ ይዞ ለመስራት እንደሚያስችል አቶ ሐፍቶም ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ የስልጠናና አቅም ግንባታ ስራዎች ዘመኑ የሚጠይቀውን ክህሎት የሚያስጨብጥ፣ ጥምር (Blended)
የስልጠና ሂደትን የተከተለ እንዲሆን ም/ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።