ኢንስቲትዩቱ በመጀመሪያ ዙር በአሽከርካሪነት ሙያ ያሰለጠናቸውን ዜጎች አስመረቀ፡፡ ****************ጥቅምት 21/2017********************

በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ‹‹ኢትዮ-ቻይና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤት›› ለውጪ አገራት ስራ ስምሪት የሰለጠኑ አሽከርካሪዎች ተመዝነው ብቁ መሆናቸው በመረጋገጡ ከኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እጅ ምስክር ወረቀታቸውን ተቀብለዋል፡፡
‹‹ዜጎች ብቁ እና በሥነ-ምግባራቸው የታነጹ ቢሆኑ ራሳቸውን ጠቅመው አገራቸውንም በበጎ ያስጠራሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከክህሎት ስልጠና በተጨማሪ በየመዳረሻዎቻቸው ‹‹ሙያዊ አምባሳደርነት›› እንዲወጡ የሚያስችላቸው ስልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተለያዩ አገራት ጋር እየፈጠረ ባለው ትስስር በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑና በከፊል የሰለጠኑ ሙያተኞችን ለመላክ በያዘው መርሃግብር አንዱ የአሸከርካሪነት ሙያ አንዱ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎቢዚያ ኢንተርራይዝ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም በአዲስ አዋቅሮ ቁሰቁሶችን አሟቶ ስልጠና በመስጠት ብቁ ዜጎችን እያፈራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ‹‹ኢትዮ-ቻይና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤት›› ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ የኋላሸት ለመጀመሪ ዙር ስልጠና ከበርካታ አመልካቾችና ተፈታኞች መካከል 140 ሰለጣኞችን ብቁ የሚያደርግ ቴክኒካዊና ባህርያዊ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡
በሥነባህርይ፣ የመንገድ ደህንነት፣ አዲስ ቴክኖሎጂ መላመድን፣ እና ዘመናዊ ተሸከርካሪዎችን መጠገን ላይ ሰልጥነዋል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ቀጣይነት እንደሚኖረው አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል፡፡