ኢንስቲትዩቱ የአቅመደካማ ቤቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ስራ ጀመረ። ***ጥቅምት 12/2017********
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ማህበረሰባዊ አገልግሎት መስጠት ከተሠጡት ተልዕኮዎች አንዱ ሲሆን ከሠሞኑ በየካ ክፍለከተማ ወረዳ 9 የሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ስራ ጀምሯል።
የኢንስቲትዩቱ የሁለተኛ ዲግሪ ሰልጣኞች ፕሮጀክቶቻቸውን ችግር ፈቺ ተግባራት ላይ እንዲውል በያዘው አቅጣጫ መሠረት እነዚህን የአቅመ ደካማ ቤቶች በሠልጣኞች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።