አውሮፓ ህብረት እና የፊንላንድ መንግስት ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ። *******ጥቅምት 7/2017****************

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር እና የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጸዳለ ተክሉ ከአውሮፓ ህብረት እና ከፊንላንድ መንግስት ተወካዮችን ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይታቸውም ትብብሮችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ነው።
ዋና ዳይሬክተሩ የፊንላንድ መንግስት በተለያዩ ፕሮጀክቶች አማካይነት ለኢንስቲትዩቱ ተልዕኮዎች ስኬት የሚያግዙ በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር ገልጸዋል። የፊንላንድ መንግስት ፕሮጀክት የሆነው Capacity Building for Modernizing TVET Pedagogy in Ethiopia (MOPEDE) ፕሮጀክት ለኢንስቲትዩቱ እና ለሌሎች ተቋማት አመራሮሮና አሰልጣኞች አቅም ግንባታ፣ በጥምር (Blended) የስልጠና ስልት ላይ ትርጉም ያለው ሥራ ሲሰራ እንደቆየም ጨምረው አብራርተዋል፡፡
የፊንላንድ ትምህርት ኤጀንሲ ከፍተኛ አማካሪ ኒና ቴንኦን ጨምሮ የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው ኢንስቲቲዩቱ ዲጂታይዜሽን ላይ እየሰራ ያለውን ስራ መመልከታቸውንና በዚህም አድናቆታቸውን ገልጸው ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡
የቀጣይ ትብብር ማዕቀፉ በተለይም በቴክኒክና ሙያ ዲጂታይዜሽን ላይ ማለትም ዲጂታል መሰረተ-ልማት ማስፋፋት እና ዲጂታል ክህሎት ላይ እንደሚተኩር ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡