#አሁን #Now

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ለሳተላይት ተቋማት አመራሮችና አሠልጣኞች ‹‹ቴክኒክና ሙያ በዓለምአቀፍ አውድ፣ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የኢንስቲትዩቱ የለውጥ ሀሳቦች›› (TVT Global context, Ethiopia’s position and TI Reform Initiatives) በሚል ርዕስ ስልጠና እየሰጡ ይገኛሉ።
የስልጠናው ዓላማም ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ በዘመናዊው ዓለም የቴክኒክና ሙያን ሁኔታ ተረድቶ ኢንስቲትዩቱን ለመለወጥ እና የሪፎርም ሐሳቦችን ለማሳካት የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።
ኢንስቲትዩቱ በሁሉም ተቋሞቹ በሁሉም አመራርና አሠልጣኞች ተመሳሳይ አመለካከት በመያዝ የዓመተ-ልህቀት እሳቤን ለማሳካት ያለመ ውይይት በተከታታይነት እያካሄደ ይገኛል።