ከአይቤክስ ቴክኖሎጂስና ፕሮሞሽን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተደረገ።

*************ጥቅምት 2/2017 *************
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ከአይቤክስ ቴክኖሎጂስና ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ ወጣት ኢዘዲን ካሚል ጋር ተቋማቱ በሁለትዮሽ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል።
ሁለቱ ተቋማት ቀደም ብለው ለትብብር ውይይት መጀመራቸውን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ስምምነት ወደ ተጨባጭ ስራ ለመቀየር ያስችላል ብለዋል።
በኢንስቲትዩቱ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን ለማስቀጠል፣ በተለይም ከወጣቶች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ አኳያ ኢንስቲትዩቱ የሚሠራቸውን ስራዎች ያጠናክራል ተብሏል።