ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ስልጠና እና የማነቃቂያ መድረክ ተካሄደ፡፡

*****************መስከረም 30/2017**************
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በዓለምአቀፋዊና አገራዊ የቴክኒክና ሙያ እሳቤዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ የስልጠና መድረክ ተካሂዷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ‹‹ቴክኒክና ሙያ ዓለምአቀፍ አውድ፣ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የኢንስቲትዩቱ የለውጥ ሀሳቦች›› (TVT Global context, Ethiopia’s position and TI Reform Initiatives) በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ብሩክ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ ሰራተኞች ዓለምአቀፋዊ እና አገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ተረድተው ኢንስቲትዩቱ የያዛቸውን የለውጥ ሀሳቦች በንቃት ለመፈፀም ስንቅ እንዲሆናቸው በማሰብ ነው ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ልህቀት ለማምጣት በ2016 ዓ/ም መሰረት መጣሉን ገልጸው በ2017 በጀት ዓመት (‹‹ዓመተ-ልህቀት 2››) እሳቤውን ለማስፋት እና ለማስቀጠል ኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በሙሉ እንደ ቤተሰብ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡