የሱንቡላ ፕሮጀክት ከኢንስቲትዩቱ ልምድ ለመቅሰም የሚያስችል ውይይት እና የመስክ ጉብኝት ተካሄደ። **************መስከረም 29/2017*********

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በወጣቷ ስራ ፈጣሪ እና የኢትዮጵያ ወጣት አንተርፕረነሮች ማህበር ፕሬዚደንት ሳሚያ አብዱልቃድር የተመራ የልዕካን ቡድንን ተቀብለው አወያይተዋል።
በልዕካን ቡድኑ ከፈረንሳይ፣ ከሱዳን፣ ከየመን እና ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ሙያተኞች የተካተቱበት ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ልምድ ለማቅሰም ያለመ ጉብኝት እያካሄዱ እንደሆነ ተገልጿል።
ዶ/ር ብሩክ በውይይቱ ወቅት ኢንስቲትዩቱ በዋናው ግቢ እና በሳተላይት ተቋማት እየሠጠ ያለውን ስልጠና አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዘርፉን ለመለወጥ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች እየተፈጠረ ያለበትን ሁኔታ የአሰራር ሁኔታዎች ገልጸውላቸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ከኢንስቲትዩቱ አልፎ እንደ አገር ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ መዘመን በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በስልጠና ጉዳዮች ላይ እየተሠራ ያለውን ሥራ አብራርተውላቸዋል።
ሱንቡላ ፕሮጀክት በግብርና መስክ የተሠማራ ዓለምአቀፍ ተቋም ሲሆን ከአውሮፓ በፈረንሳይ እና ከአፍሪካ በሱዳን እንዲሁም በሩቅምስራቅ በየመን እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን እንግዶቹ ባዩት የኢንስቲትዩቱ ስልጠና ወርክሾፖች መደሰታቸውንና ትልቅ ልምድ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።