ኢንስቲትዩቱ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚመጥኑ እና የበቁ ሙያተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ገለጹ።
ኢንስቲትዩቱ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚመጥኑ እና የበቁ ሙያተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ሐብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሁለተኛው ሲጉል የተሰጥኦ ማበልጸጊያ የስልጠና ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ተከፈተ፡፡
***************መስከረም 7/2017****************
በአፍሪካ ግዙፍ የልማት ስራ ውስጥ የተሰማራው የቻይና ኮንስትራክሽን ኮምዩኒኬሽን ካምፓኒ (CCCC) የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ታሳቢ ያደረገ ሴጉል የተሰኘ የተሰጥኦ ማበልፀጊ ፕሮግራም ከፍቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ካምፓኒው ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር በየዘርፉ ያሉ ሙያተኞችን ያሰለጥናል፡፡
ካምፓኒው የፕግራሙን ሁለተኛ ዓመት በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በይፋ ያስጀመረ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር በአራት የሙያ መስኮች አንድ መቶ ሁለት ሰልጣኞችን ለአንድ ወር የሚቆይ ስለጠና አስጀምሯል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐብታሙ ሙሉጌታ፣ በፕግራሙ መክፈቻ እና በስልጠና ማስጀመሪያ ላይ ኢንስቲትዩቱ ለዓለምአቀፍ ገበያ የሚመጥኑ እና የበቁ ሙያተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ለዚህም ተልዕኮው ስኬት እንደ ቻይና ካሉ አገራት እንደ CCCC ካሉ ካምፓኒዎች ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ይህ ዛሬ በይፋ የተጀመረው ስልጠናም ከኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ አንዱ ሲሆን የዓለማቀፍ ትብብር አካል መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል፡፡
የቲያንጂን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሰቲ የስራ ሀላፊ የሆኑት ዣንግ ጃንጋንግ በበኩላቸው የ2024ቱ ቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ በስኬት መጠናቀቁን አንስተው ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ አዙሯል ብለዋል፡፡
የቻይናንና ኢትዮጵያን ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግረው የተሰጥኦ ማበልጸጊያ የስልጠና ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ባለፈው ዓመት እንደተፈረመ የገለጹት ሀላፊው የቻይና ኩባንያዎች የሰለጠነ የሰው ሀይል እንዲያገኙ አዳዲስ እና የስራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ይሰጣሉ ብለዋል፡፡
ዛሬ የተጀመረው ስልጠናም ኢንደስትሪ የሚፈልገውን ብቁ የሰው ሀይል ለማስገኘት ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው በኢንስቲትዩቱ ለአንድ ወር የሚሰጥ ሲሆን በ Building Construction, Building Material Testing, Surveying Construction Equipment Maintenance ላይ እንደሚያተኩር በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል፡፡
የቲያንጂን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በ2021 (እ.ኤ.አ) የሉባን ወርክሾፕን ከፍቶ በሜካትሮኒክስ፣ ሮቦቲክስና አርቴፊሻል እንተሊጀንስ ለኢንደስትሪ ቴክኒሺያኖች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ከኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ፣ ከሥራና ክሀሎት ሚኒስትር፣ ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት፣ ከቻይና ኮንስትራክሽን ካምፓኒዎች፣ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረት፣ እና ከተለያዩ ድርጅቶች የስራ ሀላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡