ኢትዮጵያ በ47ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ተሳትፎዋ

ኢትዮጵያ በፈረንሳይ ሊዮን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 47ኛው ዓለምአቀፍ የክህሎት ውድድር በሦስት የውድድር መስኮች ማለትም IT Network Systems Administration (IT)፣ Cabinetmaking (Woodwork)፣ እና CNC Turning (Manufacturing) እየተሳተፈች ትገኛለች። ይህም ኢትዮጵያ ኣባል በሆነችበት ዓመት ባልተለመደ ሁኔታ ተወዳዳሪዎችን በማዘጋጀት በመወዳደር ደማቅ ታሪክ ጽፋለች።
በውድድር መድረኩ ላይ የኢንስቲትዩታችን ም/ዋና ዳይሬክተር እና የዓለም ክህሎት ውድድር አገር አቀፍ ቴክኒክ ተወካይ ሐፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር ሴክሬተሪ ቦርድ እና ጠቅላላ ጉባኤ (General Assembly) ፊት ቀርበው አገራችን የክህሎት ውድድር አባል ለመሆን የሰራችውን ቅድመ ዝግጅት፣ ለክህሎት ልማቱ የተሰጠውን ትኩረት፣ በቀጣይ የያዘችውን ዕቅድ በዝርዝር አቅርበዋል።
ጠቅላላ ጉባኤውም የቀረበውን ሁለንተናዊ አገራዊ ዝግጅትና ተፈላጊውን መስፈርት መማላቱን በማረጋገጥ የይሁንታ ድምጽ የሠጠ ሲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የይፋዊ የአባልነት ሰርተፍኬት ተቀብለዋል።
አገራችን በዚህ ዓለማቀፍ መድረክ አባል እንድትሆን እና በውድድሩ እንድትሳተፍ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ሚና ተወጥቷል።
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመሩት የልዕካን ቡድን የስራ ሀላፊዎች፣ አሠልጣኞችና ሠልጣኞች እየተሳተፉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሦስተኛ ቀን ውድድር ተጀምሯል።