2ኛዙር የሠመርካምፕ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ያዘጋጁት በአይነቱ ልዩ የሆነ የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራም ወጣቶች የፈጠራ ሐሳባቸውን እና ችሎታቸውን ወደ ተጨባጭ ስራ እንዲለውጡ በማስቻል ለአገራችን ሁለንተናዊ እድገት ትልቅ አበርክቶ ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ማስገኘት የሚያስችል ትልቅ ፕሮግራም ነው።
ለዚህ የፈጠራ ፕሮግራም ለሁለተኛ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል። ስለሆነም በማንኛውም መስክ የቴክኖሎጂ እና የሥራ ፈጠራ ሐሳብ ያላችሁ በሙሉ ከነሐሴ 27/2016 ዓ/ም ጀምሮ ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል።
ማሳሰቢያ
– ምዝገባው የሚካሄደው በተቀመጠው ድህረገጽ ብቻ ነው።
– ከምዝገባ በኋላ በሚካሄድ ልየታ መሠረት ለሚመረጡ የፈጠራ ባለሙያዎች የሠመር ካምፕ ፕሮግራሙ የሚካሄደው አዲስ አበባ ላምበረት መነሀሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ካምፓስ ነው።