ቴክኒክና ሙያ ስርዓት ላይ የሚሰራው ስራ የአገርን ኢኮኖሚ ለመለወጥ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑ ተገለፀ፡፡ ************ነሐሴ 23/2016**************

ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሀሳብ በአገርአቀፍ ደረጃ ለቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች እየተሰጠ የሚገኘው አቅም ግንባታ ስልጠና ሁለተኛ ቀን ላይ ደርሷል፡፡
ከ17 የስልጠና ማዕከላት መካከል አንዱ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሲሆን 1ሺ ሁለት መቶ የሚደርሱ አሰልጣኞች እየሰለጠኑ ይገኛሉ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የስልጠናው አበይት ዓላማዎችን በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው እና በዘርፉ አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የተቀራረበ የአመለካት ደረጃ ላይ ለማድረስ፣ አሰልጣኞች ቴክኒካዊ እና ባህሪያዊ ብቃታቸውን ለማሳደር እንዲሁም በአገራችን የቴክኒክና ሙያ ገጽታ ግንባታ ለማደግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
ቴክኒክና ሙያ የአገር መገንቢያ መሳሪያ ነው ያሉት ዶ/ር ብሩክ ዜጎች ክህሎታቸው ካደገ ለአገር ኢኮኖሚ መዳበር ወሳኝ አቅም መሆን እንደሚችሉ እና ይህንን ለማድረግ ቁልፍ ከሆኑ አካላት መካከል ደግሞ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ዋነኞቹ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተካሔደ የመዘጋጀቱ አስፈላጊነትም ይሄው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
አሰልጣኖችን ዘመኑ የደረሰበትን እሳቤ ለመጨበጥ እንደሚስችላቸው ዋና ዳሬክተሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ሁለተኛ ቀን ውሎ ሰልጣኞች በቀረበላቸው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡