በስቴም ማዕከል ከአጠቃላይ ትምህርት የመጡ ተማሪዎች የኮምፒተር ፕሮግራሚንግ ስልጠና እየወሰዱ ናቸው፡፡ ነሃሴ 15/2016 ዓ.ም.
ከስቴምፖወር ጋር በመተባበር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ሂሳብ እና ተያያዥ ችሎታ ወጣቶችና ልጆች የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ የሚያግዝ የኢንስቲትዩቱ ስልጠና ማዕከል፣ የመጀመሪያ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ከጀመረ ሳምንት ሆኗል፡፡
ተማሪዎቹ ከአጠቃላይ ትምህርት የመጡ ሲሆኑ በራሳቸው ወብሳይት እያለሙ ናቸው፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይም አንድ የማህረሰቡን ችግር የሚፈታ ነገር ሰርተው እንደሚወጡ ከአስተባባሪዋ ወ/ሮ ፋኖሴ ከበደ መስማት ችለናል፡፡





