እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ክህሎት ድርጅት አባል ሆነች
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት የአባልነት ጥያቄ አቅርባ ላለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ምላሹን ስትጠባበቅ ቆይታለች።
ይህም የቴክኒክና ሙያ ሥርዓታችን ለሀገሪቱ ልማትና ብልጽግና የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማላቅ የጀመርነውን ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ፡፡
የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ቦርድ አባላት ኢትዮጵያ የድርጅቱ ሙሉ አባል እንድትሆን ለሰጣችሁት ድምጽ እንዲሁም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሂደቱ እንዲሳካ ላበረከታችሁት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ!
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!