የISO 9001: 2015 የጥራት ደረጃ የምስክር ወረቀት ርክክብ ስነስርዓት ተካሄደ። ሃምሌ 30/2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት በተከታታይነት ያካሄደውን የጥራት ቁጥጥር ካጠናቀቀ በኋላ የISO 9001:2015 የጥራት የምስክር ወረቀት ዛሬ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት ሰጥቷል።
የጥራት የምስክር ወረቀቱን ከኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የሰርቲፊኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምሳለው እንየው እጅ የወሰዱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በሚመጣው የበጀት ዓመት ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የስልጠና እና የአስተዳደር ስራዎችን በISO 9001: 2015 የጥራት ደረጃ መሰረት የሚተገብር እንደሆነ ገልጸዋል።
ዋናው ነገር የምስክር ወረቀት ማግኘት እንዳልሆነ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ቀጣይ ስራዎችን በስታንዳርዱ መሰረት መስራት ነው ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ የስልጠና ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር ሃይሌማሪያም ንጉሱ (ዶ/ር) እንዳብራሩት ይህንን የምስክር ወረቀት ለማግኘት ሃላፊነት የተሰጠው ቡድን፣ አመራሩ፣ ሰራተኛውና አጋዥ አካላት ያለፉትን ወራት በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል።
የስልጠናና አስተዳደር ስራዎችን በደረጃው መሰረት መስመር ማስያዝ መቻሉንም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የሰርቲፊኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምሳለው እንየው በበኩላቸው ድርጅቱ የዓለምአቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ለአገልግሎት ሰጪና ለምራች ድርጅቶች እየፈተሸ በመስጠት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እያስቻለ ነው ብለዋል።
በዚህም የኢንስቲትዩቱን የስልጠና፣ የጥናትና ምርምር፣ የቴክኖሎጂና እንተርፕራይዝ ስራዎችን እነዲሁም ሌሎች የድጋፍ ሰጪነት ስራዎችን በመፈተሽ የISO 9001: 2015 ጥራት ማረጋገጫ መሰጠቱን ገልጸዋል።
በስነስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲዔታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲኖራቸው ‘ሪብራንድ’ የማድረግ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም ሲባል ወደዓለም አቀፍ የስራ ገበያ የሚቀላቀሉ ዜጎች የሚጠበቅባቸውን ደራጃ ማሟላት ሰላሉባቸው የስልጠና ተቋማትም የዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን እንዲያሟሉ ይደረጋል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ባስመዘገበው የጥራት ደረጃ ሽልማት ደስተኛ መሆናቸው የገለጹት ሚኒስትር ዲኤታው ባገሪቱ ያሉ ሁሉም የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች እና COC ማዕከላት የጥራት አስተዳደር ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ በቅርቡ እናደርጋለን ብለዋል።
+13
All reactions:

67