በኢንስቲትዩቱ በሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽንና ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት (EASTRIP) የሚካሄደው የልሕቀት ማዕከላት የግንባታ አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑን የዓለም ባንክ የሱፐር ቪዥን ቡድን ገለጸ።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዋና ዳይሬክተር ሐፍቶም ገ/እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) በዛሬው ዕለት በኢንስቲትዩቱ ከተገኙት የዓለም ባንክ የሱፐር ቪዥን ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል።
አባላቱ በኢንስቲትዩቱ የተጀመሩ የልህቀት ማዕከላት ሕንጻዎችን አፈጻጸም የተመለከቱ ሲሆን ከቀረበላቸው ሪፖርት ጋር በማመሳከር ክንውኑ በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑን እንደተመለከቱ ገልጸዋል።