የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ በልዩነት ለመስራት ኢንስቲትዩቱ ኢቭቶጵያ ከተባለ ስታርትአፕ ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ሃምሌ 23 2016 ዓ.ም.
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ኢንስቲትዩቱ ‘ከማሰልጠን በላይ’ እሳቤን ሰንቆ የቴክኖሎጂ ልማት ስራ ላይ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ያለ ኢንስቲትዩት መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ትልም መሳካት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የትብብር ማዕቀፋ ነባር መኪኖችን ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች መቀየር፤ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ስልጠና መስጠት፣ እንዲሁም ስማርት አውቶሞቲቭ ጋራጅ ለመመስረት ያለመ ሲሆን ተቋማቱ እየተጠናከሩ ሲሄዱ ደግሞ ኤሌክትሪክ መኪኖችን የመገጣጠም ከዛም የማምረት ስራ በመስራት ገበያውን ለመቀላቀል ያስችላቸዋል።
ይህ ትብብር የሥራ ፈጠራና የኤሌክትሪክ መኪና አጠቃቀምን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገባ እንደሚቀይር የተናገሩት ደግሞ የኢቭኢትዮጵያ መስራችና ስራአስኪጅ አቶ ይስሃቅ ከድር ናቸው።
አቶ ይስሃቅ ከድር ኢቭኢትዮጵያ እና ኢንስቲትዩቱ በአገራችን የኤሌክትሪክ መኪኖች መሰረተልማት መዘርጋትና የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመስራት 18 ወራትን ብቻ እንደሚፈልጉ በስምምነቱ ወቅት ገልጸዋል።