“በአንድ ድንጋይ …” የሰመር ካምፕ ቴክኖሎጂዎች ትሩፋት *************ሐምሌ 18/2016*************
ኢንስቲትዩታችን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ያዘጋጀው እና በርካታ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን ያሰባሰበው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ዘርፈብዙ አገልግሎት ያላቸው ቴክኖሎጂዎች እየተፈጠሩበት ቀጥሏል፡፡
ወጣት አህላም አሊ እና ጓደኞቿ ከየአካባቢቸው ያዩትን ችግር ለመፍታት እየሰሩ ባለው ስራ በርካታ ተግራትን በአንድ የያዘ ቴክኖሎጂ መፍጠር ችለዋል፡፡ ቴክኖሎጂው በከፊል አውማቲክ የሆነ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ እና የከሰል ማምረቻ ማሽን (Semi Automated charcoal and animal feed Machine) ይሰኛል፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ በአንድ ድንጋይ ብዙ ወፍ እንዲሉ ከአንድ በላይ መፍትሔ ይዟል ብለን የገለጽንበት ምክንያት በአገራችን ትልቁን ችግር ለመፍታት በመነሳታቸው ነው፡፡ በየቦታው በቅሎ የአፈርን ለምነት በመቀነስ ምርትና ምርታማነትን የሚቀንሰውን ለግብርናው መስክ እንቅፋት የሆነውን በሳይንሳዊ ስሙ ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ (Prosopis Juli flora) ወይም በተለምዶ ወያኔ ዛፍ በመባል የሚታወቀውን አረም ወደ እንስሳት መኖነት እና ወደከሰል ይቀይረዋል፡፡ ይህም ችግርን ወደ መፍትሐየ የቀየሩበት ትልቅ ሐሳብ ያደርገዋል፡፡
ወጣቶቹ በሰመር ካምፕ ቆይታቸው ፕሮጀክቶቻቸውን ለማጠናቀቀ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ ምሽት ድረስ ወርክሾፕ ላይ ማሳለፋቸው የስራ ባህላቸው ላይ ለውጥ እንዳመጣላቸውን ትገልጻለች፡፡
ወጣት አህላም እንደምትለው ቴክኖሎጂያቸው በአጭር ጊዜ ወደ ተጠቃሚው የሚደርስ ሲሆን ማህበራቸው ከዚህ የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በኋላም ቀጥሎ በኢንተርፕራይዝ ደረጃ እንደሚቀጥል ገልጻልናለች፡፡