ኢንስቲትዩቱ ‘ግዝሽ ኢንዱስትሪስ’ ከተባለ የማሽን አምራች ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተመካከረ። ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ሰኔ 24/2016 ዓ.ም በኢንስቲትዩታችን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) የተመራ ቡድን ዛሬ ‘ግዝሽ ኢንዱስትሪስ’ የአምራች ኩባኒያ የስራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ሲሆን በጋራ ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር አድርጓል። ኩባኒያው በቀጣይ የኢንስቲትዩቱን የስራና የምርት እንቅስቃሴ የሚመለከት ሲሆን ‘ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ’ ጋር በተለይ ሽርክና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። July 3, 2024