‹‹ቴክኖሎጂዎች፣ የምርምር ውጤቶች እና የፈጠራ ሥራዎች ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ማደግ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ›› በሚል መልዕክት ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ትውውቅ መድረክ ተካሔደ። *************ግንቦት 30/2016************

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በትብብር የሲቪል ቴክኖሎጂ ፋካሊቲን 2ኛ ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ እና የቴክኖሎጂ ማሳያ ፕሮግራም አካሄዱ።
ክቡር ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት የኮንትራክሽን ዘርፍ ለአገራችን እድገት ከፍ ያለ ሚና የሚወጣ ዘርፍ ሲሆን ከአገር ውስጥ ምርት 20 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይሸፍናል ብለዋል፡፡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ከፍተኛ የሰው ሐይል የሚሰማራበት ዘርፍ እንደሆነም አንስተዋል፡፡
እንደአገር በዘርፉ ያሉ ችግሮች በተለይም በግብአት እጥረት የሚፈጠርን የግንባታ መዘግየት ለመፍታት በመንግስት ከሚመሰሩ ስራዎች በተጓዳኝ ተቋማት በመተባበር ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማድረግ፣ ከጥናቶች የተነሱ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ክህሎቱ የዳበረ ዜጋ ማፍራት ላይም ተቋማት ተባብረው ሊሰሩ እንደሚገባ ሚንስትር ዲኤታው አሳስበዋል፡፡
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በመክፈቻ ንግግራቸው የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ዘርፍ በፍጥነት እየተለወጠ ያለ ዘርፍ ነው ያሉ ሲሆን የሚካሔዱ ጥናትና ምርምሮችን እና እየተፈጠሩ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን በተቀናጀ መልኩ ከተሰሩ ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ ያስችላሉ ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለመለወጥ ጥራት ያለው ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውሰው በተጨማሪም ተኪ ቴክኖሎጂዎችን የማምረት አበረታች ጅምሮች እንዳሉ ገልፀዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ ስራዎች በአንድ ተቋም ብቻ የሚሳኩ ባለመሆናቸው በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ ለዚህም ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር እየሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የኮንስራክሽን ማኔጅመን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ ስሜ በበኩላቸው ዘርፉን ለማዘመን ኢንስቲትዩታቸው የሚሰራውን ስራ ጠቅሰው ከተቋማት ጋር ያላቸው ትስስርም ለዚህ ትልቅ እገዛ እያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህ መድረክም ከዚህ ቀደም በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ሰስምምነት ወደተግበር የተገባበት ሁኔታ መሳያ ነው ብለዋል፡፡ መድረኩ በዘርፉ ላይ ያሉ ችግሮች ላየ ለመወያየት እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
የሰመር ካምፕ ተሳታፊዎችን ጨምሮ ዘርፉን የሚለውጡ ቴክኖሎጂዎች እና ጥናትና ምርምሮች ቀርበዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ክቡር ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ፣ የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር፣ ኢንጂነር ታምራት ሙሉ የኮንስራክሽን ማኔጅመን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣ የሁለቱ ተቋማት ም/ዋና ዳይሬክተሮች፣ አሠልጣኞች፣ የክልል ስራ ሀላፊዎች፣ በክረምት ወራት የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራም (Summer Camp) ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች እና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።
+25
All reactions:

20