ጥናትና ምርምሮች በሼልፍ ሳይወሰኑ ወደተግባር ተለውጠው አገር እንዲጠቅሙ ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

የኢንስቲትዩቱ የኤክትሪካል/ኤሌክትሮኒክስ ና አይሲቲ ካፋሊቲ 2ኛው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ በዘርፉ ያሉ የለውጥ ሐሳቦች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተካሄደ።
****ግንቦት 28/2016******
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የኤክትሪካል/ኤሌክትሮኒክስና አይሲቲ ካፋሊቲ 2ኛው ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ “Emerging Trends in Electrical, Electronics, Control, Computing, Communication, Information Technologies, and Advanced Automation.” በሚል መሪ መልዕክት ተካሔደ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር በመክፈቻ ንግግራቸው ከኢንስቲትዩቱ ተልዕኮዎች እና ለውጥ ካመጣባቸው ቁልፍ ተግባራት አንዱ ጥናትና ምርምር መሆኑን ጠቅሰው ተግባሩ ከኢንስቲትዩቱ አልፎ ለዘርፉ አዲስ ምዕራፍ ከፋች ሆኗል ብለዋል። ጥናትና ምርምርን ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነጥሎ የማየት የተዛባ አመለካከት የነበረ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በሚሰራቸው ስራዎች ይህንን እሳቤ ማረም እንደቻለ ገልጸዋል።
በዛሬው የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ እና አይሲቲ ጥናትና ምርምር ሴሚናር የሚቀርቡ ጥናቶች አገራችንን ለመለወጥ ለሚሠሩ ስራዎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ በማለት እንዲህ ያሉ ጥናቶች ከተቋም ያለፈ ፋይዳ እንዳላቸው አብራርተዋል።
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሐብታሙ_ሙሉጌታ በመልዕክታቸው የጥናትና ምርምር ስራ ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እድገት ልዩ ሚና እያበረከተ ይገኛል ብለዋል። ይህንን ሐሳብ ሲያብራሩ የገበያውን ፍላጎት በማጥናት በጥናት ላይ የተመሰረተ ስርዓተ-ስልጠና እንዲዘጋጅ፣ ጥራት ያለው ስልጠና እንዲሰጥ እና በዚህም ብቁ ዜጎች እንዲወጡ ያግዛል፤ ከችግሮች መነሻ የሆኑ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ ያስችላል፤ ከዚህም ሌላ ለፖሊሲ ዝግጅት እና ትግበራ ቁልፍ ሚና ይወጣል ብለዋል።
አይሲቲ በዘመናችን ያለው ሚና አይተኬ መሆኑን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ለግብርና፣ ለጤና፣ ለንግድ፣ ለስራ አመራር እና ለሌሎችም ዘርፎች ምርታማነትን በማሳደግ፣ ብክነትን በመቀነስ፣ ጊዜን በመቆጠብ የሚኖረው ሚና ጉልህ እንደሆነ ገልጸዋል።
ዶ/ር ሐብታሙ አያይዘውም እንደአገር የተያዘው የዲጂታል ኢትዮጵያ ትልም እንዲሳካ እንዲህ ያሉ ጥናትና ምርምሮች መዘጋጀት፣ ወደተግባርም መለወጥ የሚኖራቸው ድርሻ ጉልህ ነው ብለዋል።
የዕለቱ ቁልፍ መልዕክት አቅራቢ የሆኑት የአይሲቲ ፓርክ ዋና ስራአስፈጻሚ አቶ #ሄኖክ_አህመድ ያለንበትና የመጭውን ዘመን የቴክኖሎጂ ትሩፋቶች እንደስጋት ሳይሆን ለሠው ልጆች የመጡ መልካም አጋጣሚዎች አድርጎ መቀበል ይገባል ብለው ይመክራሉ።
አይሲቲ እና ተያያዥ የፈጠራ ሐሳቦች ያመጡልን በየዘርፉ ያሉ ለውጦች በአውቶሞቲቭ፣ በግብርና፣ በጤና ወዘተ ቅልጥፍናንና ምርታማነትን በመጨመር እድገትን እያፋጠኑ እንደሚገኙ ገልጸው በዚህ በየዕለቱ እየተሻሻለ በሚመጣው ዓለም የምንሰጠው ስልጠና የምናወጣቸው ሰልጣኞች ብቁ እና በፍጥነት የተለወጡ መሆን የግድ ይላቸዋል ለዚህም በትኩረት መስራት ይገባል ይላሉ።
እነዚህ ጥናትና ምርምሮች በሼልፍ ተቀምጠው ሳይቀሩ ወደተግባር እንዲገቡ ተቋማቸው ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አቶ ሄኖክ ቃላቸውን ሠጥተዋል።
በዕለቱ አምስት የጥናትና ምርምር ጽሁፎች ቀርበው ሰፊው ይይት ተደርጎባቸተደርጎባቸዋል።