የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት

የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩትን ጉበኙ።
ግንቦት 27/2016 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኢንስቲትዩቱን ለመጎብኘት ሲመጡ የስራና ክህሎት ሚኒስትር የተከበሩ ወ/ሮ ሙፌሪሃት ካሚል፣ ሚኒስትር ዲኤታ ተሻሌ በሬቻ (ዶ/ር)፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቀባበል አድርገዋል፡፡
የተከበሩ ብሩክ ከድርም (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በስልጠና፣በጥናትና ምርምር እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሰራ ያለውን የስራ እቅስቃሴ ለምክትል ጠ/ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
ምክትል ጠ/ሚኒስትሩም የኢንስቲትዩቱን ዲጂታል መሰረተ ልማትና የቴክኖሎጂ ማሻሻያ መርሃ ግብር እንዲሁም በኢንተርፕራይዝ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
ም/ጠ/ሚኒስትሩ በሳመር ካምፕ የቴክኖሎጂ ልማት እየተሰሩ ያሉትን ፕሮጀክቶች በመመልከታቸው መደሰታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡