የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና አመራሮች ካውንስል ፓናል ውይይት በማድረግና የቦርድ አባላትን በመምረጥ ተጠናቀቀ፡፡ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም
በስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፌሪሃት ካሚል የተከፈተውና ምክክር ስደረግበት የዋለው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ አመራሮች ካውንስል ከሁሉም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችና የክልል ቢሮ አባላትን በአባልነት በመያዝ ነው ዛሬ ምስረታውን ያደረገው፡፡
ምስረታውን የመሩት የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር ( ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ቲንክ-ታንክ ቡድን ሰብሳቢ ተሾመ ለማ (ዶ/ር) እና ሌሎች የዘርፋ አመራሮች እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ በበጀት ዓመቱ ከያዛቸው ዕቅዶች መካከል የዘርፋ ቲንክ-ታንክ ምስረታና የአመራሮች ካውንስል ምስረታ በስከት ተጠናቋል፡፡
የካውንስሉ አባላትም ስለአመሰራረቱ፣ አካሄዱ፣ የፋይናንስ ምንጩ እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያሉ ሀሳቦችን በማንሳት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ካውንስሉ ከሌሎች አገሮች አቻ ማህበራት ልምድ መውሰድ እንዳለበትና በአገራዊ እሳቤ እየቃኘ ስራውን መተግበር እንዳለበት ከአባላቱ ሀሳብ ተነስቷል፡፡
ካውንስሉ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ችግር መፍታትን ባህሉ ማድረግ እንዳለበትም በውይይቱ