‹‹ኢንስቲትዩቱ በተግባራዊ ስልጠና ያለው ልምድ እና የተደራጀ ተቋማዊ ብቃት በጋራ ለመስራት እንድናቅድ አነሳስቶናል›› (ዶ/ር ሐሰን የሱፍ-የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት) **************ግንቦት 22/2016***************
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ትብብሩ በአጫጭርና በመደበኛ ፕሮግራም ተግባራዊ የስልጠና መስክ፣ ተኪ ቴክኖሎጂን በስፋት የማምረት ስራ ላይ፣ ኢንተርፕረነሪያል ተቋም ግንባታ ላይ እንዲሁም የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ያስችላል ብለዋል፡፡ በእነዚህ መስኮች የኢንስቲትዩቱን አቅም ምን እንደሚመስል አብራርተዋል፡፡
በዚህ ስምምነት የተጠቀሱ ጥቅል ተግባራት በቀጣይ የአፈጻጸም ዕቅድ ይዘጋጅላቸዋል ተብሏል፡፡
ዶ/ር ሐሰን የሱፍ ዩኒቨርሲቲያቸው በአዲሱ ልየታ መሰረት አፕላይድ ዩኒቨርሲቲዎች ምድብ ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው የተግባር ተኮር ስልጠናዎች ላይ የበለጠ ትኩረት የሚያደርጉ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲያችን በመስኩ ልድ ካላቸው ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በተግባራዊ ስልጠና የዳበረ ልምድ ያለው በመሆኑ፣ የስልጠና ወርክሾቹ ዘመኑ በደረሰባቸው የስልጠና ቁሳቁሶች የተደራጁ በመሆናቸው አብረን ብንሰራ ሰፊ ልምድ እንቀስምበታለን ብለን እናምናለን ብለዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ካቋቋመው ኢንተርፕራይዝም ሰፊ ትምህርት እንደሚያገኙ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚደንቱ የኢንስቲትዩቱን የስልጠና ወርክሾፖች እና የቴክኖቢዚያ የኢንደስትሪ ውጤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝን የቴክኖሎጂ ምርት ሒደት ጎብኝተዋል፡፡





