ኢንስቲትዩቱ፣ ከአምስት ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ዘመናዊ የሥራ አመራር ስልጠና ማዕከል ለመመስረት ውይይት አካሄደ። *************ግንቦት 19/2016******

የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና አምስት ዓለምአቀፍ ተቋማት በትብብር ዘመናዊ የሥራአመራር የስልጠና ማዕከል ለመክፈት የሚያስችላቸውን ዝግጅት ጀምረዋል።
በዛሬው ዕለት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር ከኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ እና ከሲድ ፕሮጀክት የስራ ሀላፊዎች ጋር በእቅዱ አተገባበር ዙሪያ መክረዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ፣ ከአሜሪካ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፣ ከሲድ ፕሮጀክት፣ ከአንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት እና ከሆፕ ኮሌጅ ጋር በአንድነት የሚመሰርቱት ዘመናዊ የስልጠና ማዕከል የዜጎችን ክህሎት በማስፋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል።
ዶ/ር ብሩክ ከድር ቀደም ብሎ ፕሮጀክቱ ላይ ውይይት መደረጉን ጠቅሰው ከውይይቱ በኋላ ቅድመ ዝግጅቶች መጀመራቸውን ለምሳሌም ስልጠና መሠጠቱን፣ ፖሊሲ ማንዋል መዘጋጀቱን አንስተዋል።
ሁሉም ባለቤት ተቋማት የተቆጠረ እና የሚታወቅ የስራ ክፍፍል እንዲኖራቸው ይደረጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ድርሻውን ለመፈጸም ሙሉ ዝግጁነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል፤ የሥራአመራር ልማት ማዕከል የማጠናከር፣ በአስፈላጊ ግብአቶች የማሟላት ስራ ይሰራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ እና የሲድ ፕሮጀክት የስራ ሀላፊዎችም ለማዕከሉ መቋቋም ስኬት የኢንስቲትዩቱ ድርሻ ጉልህ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸው በየተቋሞቻቸው የድርሻቸውን እንደሚወጡ ቃላቸውን ሰጥተዋል