የኢፌዲሪ ቴክክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ
#ኤልያስ_አዋቶ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ
#መአዛ_አበራ ጋር ሁለቱ ተቋማት አብረው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በሁለቱ
ተቋማት ያሉ ተቋማዊ አቅሞችን በማስተሳሰር ተኪ ቴኖሎጂዎችን በስፋት ለማምረት የሚያስችል መደላድል ለመፍጠር፣ በአቅም ግንባታ፣ በጥናትና ምርምር ስራዎች አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ውይይት አድርገዋል፡፡
አቶ ኤልያስ አዋቶ የመሩት የሀላፊዎች እና ሙያተኞች ቡድን በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የመስክ ጉብኝት አድርጓል፡፡